
Episode #48
ንግድ፣ ውሃ እና የራስን እድል በራስ መወሰን፡ አፍሪካ የዘላቂ ልማት መሠረቶችን መገንባት ትችላለች?
የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና አፍሪካን አንድ የንግድ ገበያ ለማድረግ ያለመ ቢሆንም፣ ስምምነቶች ብቻ ንግድን አያሳድጉም። ንግድ እንዲያድግ የገንዘብ አቅም፣ ተስማሚ የሕግና የቁጥጥር ሥርዓት እና በአፍሪካ ገበያዎች መካከል የሚፈጠሩ የንግድ ትስስሮች ያስፈልጋሉ። “የውሃ ሉዓላዊነት ማለት መሠረተ ልማቱ፣ የገንዘብ አቅሙ እና የውሃ ሀብትን በራስ አቅም ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም ግንባታ መኖር ማለት ነው። ማን ያቅዳል፣ ማን ይከፍላል እና ማን ይጠግናል የሚሉት ጉዳዮችም በአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል እና ለህዝብ ተጠያቂ በሆነ መንገድ መረጋገጥ አለባቸው።” ሲሉ ከፍተኛ የውሃ ሀብት አማካሪው ወንዱ ፍሰሃ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ነጠላ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ከንግድ ባለፈ በዘላቂ ልማት እና በውሃ ሉዓላዊነት ዙሪያ ያላቸውን ቁርኝት እንቃኛለን። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ከቡር ገና እንዲሁም የሞርክ ዋተር የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ተወካይ ወንዱ ፍሰሃ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

